አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ቁሳቁሶች በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች በሚገኙ የምርጫ ክልሎች ደርሰዋል አለ።
የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላተወርቅ ኃይሉ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የተከናወኑ የዝግጅት ተግባራትና ቀጣይ ሂደቶች ዙሪያ ለመገናኛ ብዙሀን መግለጫ ሰጥተዋል።
ምርጫው በሚከናወንበት ግንቦት 24 ከወሳኝ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ውጪ ሁሉም የስራ ቦታዎች ዝግ ሆነው መራጮች ድምፅ ይሰጣሉ ብለዋል።
የድምፅ መስጫ ካርዶች ህትመት ተጠናቅቆ ለስርጭት ዝግጁ መሆናቸውን አንስተዋል።
ከ10 ሺህ በላይ እጩዎች መመዝገባቸውንና 80 የሚሆኑ እጩዎች የተቀመጠውን መስፈርት ማሟላት ባለመቻላቸው ከውድድር ውጭ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በድምጽ መስጫው ዕለት በየትኛውም የፖለቲካ ፓርቲዎች አባል ያልሆኑ ሦስት ቅሬታ ሰሚ አካላት በምርጫ ክልሎች እንደሚኖሩ ጠቁመዋል፡፡
በዙፋን አምባቸው

