Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ምርጫው ሀገረ መንግሥታዊ ሥርዓታችን የሚጠናከርበት መሰረት ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዘንድሮው ጠቅላላ ምርጫ ሀገረ መንግሥታዊ ሥርዓታችን የሚጠናከርበት መሰረት ነው አሉ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለዒድ አል አድሐ (ዐረፋ) በዓል ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት እንዳሉት፥ ማኅበረሰባዊ ትሥሥርና ትብብር ለዜጎችና ለሀገር ደኅንነት ወሳኝ ናቸው።

ማኅበራዊና የዜግነት ግዴታዎችን ከምንወጣባቸው የዴሞክራሲ መገንቢያ መሳሪያዎች መካከል ዋነኛው ምርጫ ነው ብለዋል፡፡

የዘንድሮው ጠቅላላ ምርጫ የሀገሪቱ የቀጣይ ዓመታት እጣፈንታ የሚበየንበትና ሀገረ መንግሥታዊ ሥርዓት የሚጠናከርበት መሰረት መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

በተጨማሪም ብዝሃ ድምጽ የሚሰማበት የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ለመመስረት ወሳኝ አጋጣሚ መሆኑን ገልጸው፥ የዴሞክራሲ ልምምድን አንድ ደረጃ ከፍ ያደርጋል ነው ያሉት፡፡

በመሆኑም የዜግነት ግዴታን ለመወጣት ብቻ ሳይሆን በምርጫ ካርድ ዴሞክራሲያዊ መብትን ለማረጋገጥ በመዘጋጀት በዓሉን ማክበር እንደሚገባ አሳስበዋል።

Exit mobile version