Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የዒድ አል አድሃ በዓል በሀረሪ ክልል እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 1 ሺህ 447ኛው የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሀረሪ ክልል በድምቀት እየተከበረ ነው።

በዓሉን በክልሉ የሚገኙ የእምነቱ ተከታዮች ሀረር ከተማ በሚገኘው ኢማም አህመድ ስታዲየም በመሰባሰብ በተክቢራ፣ በሶላት እና በሌሎች ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶች እየተከበረ ይገኛል፡፡

በአከባበር ስነ ሰርዓቱ የክልሉ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አብዱሰላም ጂብሪል÷ ህዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከበር እርስ በርስ በመደጋገፍ ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡

በበዓሉ አከባበር ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

በተስፋዬ ሀይሉ

Exit mobile version