Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

መጪው ትውልድ የሚጠቀምበትን የግብርና እምቅ አቅም እያዘጋጀን እንገኛለን – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) መጪው ትውልድ የሚጠቀምበትን የግብርና እምቅ አቅም እያዘጋጀን እንገኛለን አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ ግዙፉ የገልጨት-ሰሪቴ የውኃ አቅርቦት ፕሮጀክት ለኅብረተሰቡ አስተማማኝ የንጹሕ ውኃ አቅርቦት ተደራሽ በማድረግ፣ በምሥራቅ ቦረና እና በቦረና ዞኖች የሚገኙ ነዋሪዎችን ሕይወት እየቀየረ ይገኛል ብለዋል።

‎በብዙ ኪሎ ሜትሮች የሚቆጠሩ የቧንቧ መስመሮችን፣ ዘመናዊ የውኃ ማከፋፈያ ጣቢያዎችን እና ሰፋፊ የውኃ ማጠራቀሚያዎችን ያካተተ ዘላቂ መሠረተ ልማት እየገነባን ሲሆን÷ ይህም ድርቅን ከመመከት የላቀ ፋይዳ አለው ነው ያሉት።

‎የሕዝብ ጤናን እየጠበቅን፣ የነዋሪዎችን መተዳደሪያ አቅም እያጠናከርን መጪው ትውልድ የሚጠቀምበትን የግብርና እምቅ አቅም እያዘጋጀን እንገኛለን ሲሉም አስገንዝበዋል።

Exit mobile version