Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የምርጫ ወረቀት የማይሰጠውና ጣቱን የድምፅ ሰጪነት ቀለም የማይቀባው ማን ነው?

1. ማንኛውም ምርጫ ጣቢያ የተገኘ መራጭ የመራጮች ምዝገባ መታወቂያ ካርዱን እና የማንነት ማረጋገጫ ሰነድ ለተመዘገበበት ምርጫ ጣቢያ የመዝገብ ሹም በማቅረብ ስሙ በመዝገቡ ላይ እንዲታይለት ይጠይቃል።

2. የመዝገብ ሹሙም፡-
ሀ) የመራጮች ምዝገባ መታወቂያ ካርዱ በምርጫ ጣቢያው የተሰጠ መሆኑን፣

ለ) የመራጩን ማንነት የሚያረጋግጥ መታወቂያ ወይም መለያ ወረቀት አብሮ የቀረበ መሆኑን፣

ሐ) በካርዱ ላይ በተመዘገበው የመዝገብ ገጽ እና ተራ ቁጥር እንዲሁም የመራጭ መለያ ቁጥር መሰረት ሙሉ ስሙ በመዝገቡ ላይ በትክክል የሰፈረ መሆኑና፣

መ) የድምጽ ሰጪነት ቀለም ያልተቀባ መሆኑን ያጣራል፡፡

3. የምርጫ ጣቢያው የመዝገብ ሹሙ መራጭ ድምጽ የሰጠ መሆኑን ለማመልከት ከድምፅ መስጫ ወረቀት አዳዩ ድምፅ መስጫ ወረቀት ከመቀበሉ አስቀድሞ በግራ እጅ አውራጣቱ ጥፍር ግርጌ፣ የግራ አውራጣት ከሌለው በሌላ ማናቸውም የግራ እጅ ጣት፥ ማናቸውም የግራ እጅ ጣት ከሌለው በቀኝ አውራጣት ግርጌ ይህም ከሌለ በማናቸውም ሌሎች የቀኝ እጅ ጣት ጥፍር ግርጌ ላይ የማይለቅ ቀለም ይቀባል፡፡

4. መራጩ የእጅ ጣት የሌለው ከሆነ የመዝገብ ሹሙ አለመምረጡን ካረጋገጠ በኋላ ከመራጩ ጋር በመስማማት በቀላሉ የሚታይ ቦታ ላይ የማይለቅ ቀለም ይቀባና እንዲመርጥ ያደርጋል፡፡

5. መራጩ የማይለቅ ቀለም ከተቀባ በኋላ የምርጫ አስፈጻሚው በመራጭ መዝገብ ላይ ለዚሁ በተዘጋጀው አምድ ላይ መራጩ እንዲፈርም ያደርጋል።

6. የእጆቹን ጣቶች ለምርጫ አስፈፃሚው ለማሳየት ወይም ቀለም ለመቀባት ፈቃደኛ ያልሆነ መራጭ የድምፅ መስጫ ወረቀት አይሰጠውም፣ መምረጥም አይችልም።

7. ድጋፍ ለሚፈልጉ መራጮች ድጋፍ ለመስጠት አብረው የመጡ ሰዎች ድምፅ የሚሰጡ ካልሆነ በስተቀር ጣታቸውን ቀለም አይቀቡም።

Exit mobile version