Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በአሰላ የምርጫ ክልል የምርጫ ቁሳቁስ እየተሰራጨ ነው

‎አዲስ አበባ፣ ግንቦት 21 ፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአሰላ ምርጫ ክልል ለሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች የምርጫ ቁሳቁስ የማከፋፈል ስራ ተጀምሯል።

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የፊታችን ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚካሄድ ይታወቃል።

‎በዚህም ለምርጫው አስፈላጊ ዝግጅቶች በየምርጫ ክልሎቹ እየተካሄደ ይገኛል።

በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የአሰላ የምርጫ ክልል ኃላፊ አቶ አለማየሁ ጋላን ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንዳሉት÷ የምርጫ ቁሳቁስ በተገቢው ጥንቃቄ ለምርጫ ጣቢዎች እየተከፋፈለ ነው።

‎በአሰላ ምርጫ ክልል 108 የምርጫ ጣቢያዎች መኖራቸውን ገልጸው÷ ‎ምርጫው ሰላማዊና ፍትሃዊ እንዲሆን የበኩላቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል።

‎በአብደላ አማን

Exit mobile version