Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የድምጽ መስጫ ቁሳቁስ የማሰራጨት ስራ በጅማ ከተማ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 21፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በጅማ ከተማ የድምጽ መስጫ ቁሳቁስ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች የማሰራጨት ስራ እየተከናወነ ነው።

የከተማዋ ምርጫ ክልል ጽህፈት ቤት ኃላፊ ነብያት አብርሃም በጽሕፈት ቤቱ ስር ለሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች የቁሳቁስ ስርጭት እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።

በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች ለድምፅ አሰጣጡ ሂደት መሳካት የተሟላ ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል።

በዚሁም ለድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ አስፈላጊ የሆኑት የድምፅ መስጫ ሳጥኖች፣ የምርጫ ወረቀቶች፣ የመመዝገቢያ ወረቀት ማህተሞች እና ሌሎች አስፈላጊ ቁሳቁሶች በከተማው ስር በሚገኙ ሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች በወቅቱና በሰዓቱ እንዲደርሱ እየተደረገ ነው ብለዋል።

በምርጫ ክልሉ 117 የምርጫ ጣቢያዎች እንዳሉ ጠቁመው÷ ለአብዛኛው ጣቢያዎች ቁሳቁስ ተደራሽ መደረጉን መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

Exit mobile version