አዲስ አበባ፣ ግንቦት 21 ፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተለያዩ የምርጫ ክልሎች የምርጫ ቁሳቁስ ሥርጭት መካሄድ ጀምሯል፡፡
የአሶሳ ሆሃ እና የአሶሳ መገሌ የምርጫ ክልሎች ለየምርጫ ጣቢያዎቻቸው የምርጫ ቁሳቁስ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች በማሰራጨት ላይ ይገኛሉ፡፡
የአሶሳ ሆሃ የምርጫ ክልል አስተባባሪ አቶ እሱባለው ንጋቱ እና የአሶሳ መገሌ አስተባባሪ አቶ ሀብታሙ ተስፋዬ እንዳሉት÷ እስከ ግንቦት 22 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በሁሉም ጣቢያዎች ቁሳቁስ አሰራጭቶ ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሠራ ነው፡፡
በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች ከሚገኙ ማዕከላት ወደ ሁሉም ጣቢያዎች የምርጫ ቁሳቁስን በወቅቱ ተደራሽ ለማድረግ ሰፊ ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝም አመልክተዋል፡፡

