Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ድምጻችንን በመስጠት ኃላፊነታችንን እንወጣለን – የቦንጋ ከተማ ነዋሪዎች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 21 ፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በመጪው ሰኞ በሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምጻችን በመስጠት ኃላፊነታችንን እንወጣለን አሉ የቦንጋ ከተማ ነዋሪዎች።

ወጣት አክሊሉ ኃይለማርያም እና ብርሃን አሰፋ እንዳሉት÷ በዴሞክራሲያዊ ምርጫ የአንድ ሰው ድምፅ ዋጋ እንዳለው በመረዳት በምርጫው ቀን ድምጻቸውን በመስጠት መብታቸውን ለመጠቀም ተዘጋጅተዋል።

የድምፅ መስጫ ቀኑን በጉጉት እየጠበቁ መሆናቸውን የገለጹት ነዋሪዎቹ÷ ምርጫ ሀገርና ሕዝብን የሚያሻግር መንግሥት በሰላማዊ መንገድ ለመመስረት ወሳኝ በመሆኑ ይህን ታልቅ ኹነት በአግባቡ መጠቀም ይገባል ብለዋል።

ምርጫ ለዴሞክራሲ ግንባታ፣ ለሀገር ሰላምና እድገት ያለው አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑን የገለጹት ደግሞ ወ/ሮ ትዝታ ፀጋዬ እና አቶ ኬሮ ጋዎ ናቸው።

ለስኬቱ የሁሉም ዜጎች ንቁ ተሳትፎ አስፈላጊ እንደሆነ አንስተው÷ በጠቅላላ ምርጫ የመምረጥ መብታቸውን በመጠቀም የዚህ ታሪካዊ ሂደት አካል እንደሚሆኑ ገልጸዋል።

የአንድ ሰው ድምጽ ዋጋ እንዳለው በመገንዘብ ዜጎች በምርጫው በመሳተፍ በኢትዮጵያ መፃኢ ዕድል ለይ መወሰን አለባቸው ሲሉም ተናግረዋል።

የከተማዋ ነዋሪዎች በመጪው ሰኞ በሚካሄድ ምርጫ ድምጻቸውን በመስጠት ሀገራዊ ኃላፊነታቸውን እንደሚወጡም መግለጻቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።

Exit mobile version