Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሸገር ከተማ ፋሲል ከነማን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 21፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ34ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሸገር ከተማ ፋሲል ከነማን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡

በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ምሽት 12 ሰዓት ላይ በተደረገ ጨዋታ ሄኖክ አዱኛ ባስቆጠረው ግብ ሸገር ከተማ ሶስት ነጥብ ይዞ ወጥቷል።

ቀደም ሲል በተደረገ ጨዋታ ሆሳዕና እና ምድረ ገነት ሽረ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡

በአዲስ አበባ ስታዲየም ቀን 7 ሰዓት ላይ መደረግ ጀምሮ 34ኛው ደቂቃ ላይ የተቋረጠው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ጨዋታ በነገው ዕለት 3 ሰዓት ከ30 በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ይደረጋል።

በተመሳሳይ ስታዲየም ቀን 10 ሰዓት ላይ ሊደረግ የነበረው የወላይታ ድቻ እና ነገሌ አርሲ ጨዋታ ግንቦት 27 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንደሚደረግ ተመላክቷል፡፡

በተጨማሪም ግንቦት 22 ቀን 2018 ዓ.ም የሚደረጉ የአዲስ አበባ ስታዲየም መርሐ ግብሮች በተያዘላቸው ሰዓት የቦታ ለውጥ ተደርጎባቸው በአበበ ቢቂላ ስታዲየም የሚካሄዱ ይሆናል፡፡

Exit mobile version