Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢጋድ በ7ኛው የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ 26 የምርጫ ታዛቢዎችን አሰማርቷል

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለስልጣን (ኢጋድ) በ7ኛው የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ በተለያዩ አካባቢዎች 26 የምርጫ ታዛቢዎች አሰማርቻለሁ አለ።

በኢጋድ የሰላምና ደህንነት ዘርፍ ዳይሬክተር ኮማንደር አበበ ሙሉነህ እንዳሉት÷ በኢትዮጵያ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ የሚታዘቡ አካላት ተሰማርተዋል።

ከኢጋድ ሴክሬታሪያትና አባል ሀገራት የተውጣቱ 26 ታዛቢ ሙያተኞች የምርጫ ሂደቱን እንዲታዘቡ ማሰማራቱን አስታውቀዋል።

የምርጫ ታዛቢዎችም በአፍሪካ ሕብረት የምርጫ ታዛቢዎች መተዳደሪያ ደንብ መሰረት ከአባል ሀገራት የምርጫ ቦርድና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች፣ ወጣቶችና ሴቶች አደረጃጀቶች ጋር በቀጥታ የሚሰሩ ሙያተኞች መሆናቸውን ገልጸዋል።

በዚህም በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የተሰማሩ ታዛቢዎች የምርጫ ቦርድ ሙያተኞችና ኃላፊዎች ጭምር በተመረጡ አካባቢዎች የታዛቢነት ስምሪት መሰጠቱን ተናግረዋል።

በዚህ ዓመት ብቻ የኡጋንዳንና ጂቡቲን የአባል ሀገራት የምርጫ ሂደት መታዘቡን ጠቁመው÷ በአሁኑ ወቅት 7ኛውን የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ እየታዘበ እንደሚገኝ አስንተዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለጠቅላላ ምርጫው በሚያደርገው ቅድመ ዝግጅት የታዛቢነት መስፈርት በማሟላት ምዝገባ አካሂደውና ቃለ ማሃላ በመፈፀም ወደ ሥራ መግባቱንም አብራርተዋል።

ምርጫ ቦርድ ለምርጫ ታዛቢነት ለተዘጋጁ አካላት የኢትዮጵያን የምርጫ ሕግና ሌሎች የአሰራር ደንቦችን የተመለከተ ስልጠና በመስጠት ፈቃድ መስጠቱን መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

Exit mobile version