Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በጎንደር ከተማ ለድምፅ መስጫ ጣቢያዎች የምርጫ ቁሳቁስን የማጓጓዝ ሥራ ተጀምሯል

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በጎንደር ከተማ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለድምፅ መስጫ ጣቢያዎች አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁስ የማጓጓዝ ሥራ ተጀምሯል።
በከተማዋ በሚገኙ የምርጫ ክልሎች ስር ላሉ 240 ምርጫ ጣቢያዎች የምርጫ ቁሳቁስ የማድረስ ሂደት በጥንቃቄ እየተከናወነ ይገኛል።
የቅድመ ምርጫ ዝግጅቱ በተያዘው መርሐ ግብር መሰረት ያለምንም እንከን እየተከናወነ ሲሆን÷ ስራው በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቅቆ ለምርጫው ቀን ዝግጁ እንዲሆን እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል።
ቁሳቁስ ከተከማቹበት ማዕከል ወደ ምርጫ ጣቢያዎች በሰላማዊ መንገድ እንዲዳረሱ አስፈላጊው የጸጥታ እና የሎጂስቲክስ ቅንጅት እየተደረገ ይገኛል።
ስራው እስኪጠናቀቅ ድረስ አስፈላጊው ክትትል ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የተገለጸ ሲሆን÷ የመራጮች መረጃ እና የድምፅ መስጫ ወረቀቶች በአስተማማኝ ሁኔታ መድረሳቸውን ለማረጋገጥ የማጣራት ሥራው በትኩረት እየተከናወነ ስለመሆኑም ተመላክቷል።
በግዛቸው ግርማዬ
Exit mobile version