Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሚወክለንን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ ድምጽ የሚሰጥበትን ቀን በጉጉት እየጠበቅን ነው አሉ የበደሌ ከተማ ነዋሪዎች።

የበደሌ ከተማ ነዋሪዎች ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንዳሉት÷ ዜጎች ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የወሰዱት የምርጫ ካርድ እንዳይባክን በአግባቡ ሊጠቀሙበት ይገባል፡፡

ነዋሪዎቹ በምርጫ ካርዳቸው የሚወክላቸውን ፓርቲ ለመምረጥ ድምጽ የሚሰጥበትን ቀን በጉጉት እየጠበቁ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

ድምጻቸው በሀገሪቱ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ሒደት ውስጥ ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

ምርጫው ዴሞክራሲያዊ፣ ፍትሃዊና ተአማኒ ሆኖ በስኬት እንዲጠናቀቅ የበኩላቸው ሚና እንደሚወጡ አመልክተዋል፡፡

የምርጫ ካርድ የወሰዱ ዜጎች በምርጫ ቀን ድምጻቸውን በመስጠት ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል።

በጋላና ተስፋ

Exit mobile version