አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአፋር ክልል በሚገኙ የተለያዩ ምርጫ ጣቢያዎች የምርጫ ቁሳቁስ ሥርጭት እየተካሄደ ነው።
ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አጋዥ የምርጫ ቁሳቁስ የማጓጓዙ ሥራ ቀደም ብሎ በክልሉ የተጀመረ ሲሆን÷ እስከነገ ሙሉ ለሙሉ የማጠናቀቁ ስራ እንደሚከናወን ተገልጿል፡፡
ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቅኝት ባደረገበት የአብአላ የምርጫ ክልል አጠቃላይ 59 ጣቢያዎች የሚገኙ ሲሆን÷ ከእነዚህ ውስጥም ለ35ቱ ሙሉ ለሙሉ ቁሳቁስ የማሰራጨቱ ስራ ተጠናቋል።
ቀሪ 24 ጣቢያዎች ደግሞ በአቅራቢያ የሚገኙ በመሆኑ እስከነገ ረፋድ ሙሉ ለሙሉ የቁሳቁስ ሥርጭቱ የሚጠናቀቅ መሆኑን የምርጫ ክልሉ መረጃ ያመላክታል፡፡
አብአላ ምርጫ ጣቢያ አጠቃላይ 3 ቀበሌዎችን ያቀፈ ሲሆን÷ በዚህም 45 መደበኛ እና 14 ንዑስ ጣቢያዎች በድምሩ 59 የምርጫ ጣቢያዎች ይገኛሉ።
በአሸብር ካሳሁን

