Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በምርጫ ካርዳችን ለምንፈልገው ፓርቲ ድምጻችንን ለመስጠት ተዘጋጅተናል – የደሴና ታርጫ ከተማ ነዋሪዎች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በወሰድነው የምርጫ ካርድ ይጠቅመናል ለምንለው ፓርቲ ድምጻችንን ለመስጠት ተዘጋጅተናል አሉ የደሴና ታርጫ ከተማ ነዋሪዎች፡፡
ነዋሪዎቹ÷ የፊታችን ሰኞ በሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ላይ በንቃት በመሳተፍ ሕገ መንግሥታዊና ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን ለማስከበር ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
በዕለቱ የምርጫ ካርዳቸውን ለሀገርና ሕዝብ ይጠቅማል ብለው ያመኑበትን የፖለቲካ ፓርቲ እንደሚመርጡ አረጋግጠዋል፡፡
ዜጎች የወሰዱትን የምርጫ ካርድ በአግባቡ በመጠቀም በሀገረ መንግሥት ግንባታ ሒደት ላይ የዜግነት ኃላፊነታቸውን መወጣት እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል፡፡
Exit mobile version