አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚወክለንን ፓርቲ ለመምረጥ የምርጫ ቀኑን በጉጉት እየጠበቅን ነው አሉ የባቱ እና አሰላ ከተማ ነዋሪዎች።
ነዋሪዎቹ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንዳሉት÷ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሀገሪቱን ነፃነትና መልካም ስም ከማስፈን አንጻር ትልቅ ሚና አለው፡፡
የሚወክለንን ፓርቲ የምንመርጥበትን ቀን በጉጉት እየጠበቅን ነው ያሉት ነዋሪዎቹ÷ ለሀገር ግንባታና ዴሞክራሲ የአንድ ሰው ድምፅ ወሳኝ መሆኑን አመልክተዋል፡፡
ሀገርን የሚጠቅምና የሚገነባ እንዲሁም የዜጎችን ሕይወት ያሻሽላል የሚሉትን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ ቁርጠኛ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡
ምርጫው ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ተአማኒ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን እንደሚወጡም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
በአብደላ አማን

