Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በምርጫው ድምጽ ለመስጠት ተዘጋጅተናል – የአለታወንዶ ከተማ ነዋሪዎች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ነገ በሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምጻችንን በመስጠት ሀገራዊ ሃላፊነታችንን ለመወጣት ተዘጋጅተናል አሉ የአለታወንዶ ከተማ ነዋሪዎች ፡፡

የከተማው ነዋሪ ዳንኤል ቀቀቦ፤ በነገው እለት በካርዳቸው ለሀገር እድገት ይበጃል የሚሉትን ፓርቲ በመምረጥ ታሪካዊ አሻራቸውን እንደሚያሳርፉ ተናግረዋል።

የከተማው ነዋሪ ወጣት መሰለ በራሳ በበኩሉ በምርጫ ሲሳተፍ ዘንድሮ የመጀመሪያው መሆኑን ገልጾ፤ ለወጣቱ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ትኩረት አድርጎ ለሚሰራ ፓርቲ ድምጽ እንደሚሰጥ ጠቅሷል።

ወይዘሮ አበራሽ ሙንጣሻ እና አቶ ዝናቡ ዳንጊሶ የተባሉ ነዋሪዎችም÷ አንድ ድምጽ ዋጋ እንዳለው በመረዳት በካርዳቸው ይበጀናል የሚሉትን ፓርቲ ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።

ለዚህም ነገ ማለዳ በምርጫ ጣቢያ በመገኘት ድምጻቸውን በመስጠት ሀገራዊ ሀላፊነታቸውን እንደሚወጡ መግለፃቸውን አዜአ ዘግቧል፡፡

#ኢትዮጵያ #ኢትዮጵያትመርጣለች #በምርጫብቻ #ፋናዲጂታል #Election #fanadigital #Ethiopia #Ethiopiavotes #Democracy #fanatelevision.

Exit mobile version