Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በምርጫው በመሳተፍ ለሀገር ግንባታ የበኩላችንን እንወጣለን – የሰቃ ጨቆርሳ ወረዳ ወጣቶች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በጅማ ዞን የሰቃ ጨቆርሳ ወረዳ ወጣቶች በዴሞክራሲያዊ ምርጫ ላይ በመሳተፍ ለሀገረ መንግሥት ግንባታ የበኩላችንን አስተዋጽኦ እንወጣለን አሉ።

ወጣቶች በነገው እለት በሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ የወሰዱትን ካርድ ተጠቅመው ለሀገር የሚበጀውን ፓርቲ ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።

ሌሎች ወጣቶችም በምርጫው በመሳተፍ የኢትዮጵያን አሸናፊነትን ማረጋገጥ እንደሚገባቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።

በሰቃ ጨቆርሳ ምርጫ አንድ ክልል 104 ምርጫ ጣቢያዎች የምርጫ ቁሳቁስ በጊዜ የማሰራጨት እና ሌሎች የቅደመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸውን የምርጫ ክልሉ አስተባባሪ አቶ ሁሴን አባቢያ ተናግረዋል።

በወርቅአፈራው ያለው

#ኢትዮጵያ #ኢትዮጵያትመርጣለች #በምርጫብቻ #ፋናዲጂታል #Election #fanadigital #Ethiopia #Ethiopiavotes #Democracy #fanatelevision

Exit mobile version