Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በጉራጌ ዞን ጉመር ቁጥር 1 ምርጫ ክልል የድምፅ መስጫ ቁሳቁስ ተሰራጨ

‎አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን የጉመር ቁጥር 1 ምርጫ ክልል ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚውሉ የድምፅ መስጫ ቁሳቁስ ስርጭት ተከናውኗል፡፡

‎‎በጉመር ቁጥር 1 ምርጫ ክልል ሥር 46 የምርጫ ጣቢያዎች የሚገኙ ሲሆን ለእነዚህ ጣቢያዎች አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶችን በተሽከርካሪዎች የማድረስ ሥራ እየተከናወነ ይገኛል።‎

‎የጉመር ቁጥር 1 ምርጫ ክልል ኃላፊ አቶ ሙባረክ ያሲን÷ የምርጫ ቁሳቁሶቹን በየምርጫ ጣቢያዎቹ የማድረሱንና ተደራሽ የማድረጉን ሥራ እስከ 7 ሰዓት ድረስ ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል።

#ኢትዮጵያ #ኢትዮጵያትመርጣለች #በምርጫብቻ #ፋናዲጂታል #Election #fanadigital #Ethiopia #Ethiopiavotes #Democracy #fanatelevision.

Exit mobile version