Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

እየመረጠች እያለ ምጧ የመጣው እናት…

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ በመሳተፍ ላይ ሳለች በምጥ የተያዘችው ነፍሰ ጡር ድምጿን ሰጥታ ወደ ሆስፒታል አምርታለች።

የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ በነቂስ ወጥተው በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

በከተማዋ ሜሪጆይ ህዳሴ ምርጫ ጣቢያ ድምጿን ለመስጠት የተገኘችው ወ/ሮ ማህሌት ወልዴ ለመምረጥ ተዘጋጅታ ሳለ ነበር ድንገት በምጥ የተያዘችው።

በዚህም ነዋሪዋ ለሚቀጥሉት 5 ዓመታት ይበጃል ለምትለው ተመራጭ ድምጿን ሰጥታ በአቅራቢያዋ ወደሚገኝ የጤና ተቋም አምርታለች።

Exit mobile version