አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ምርጫው ዜጎች ሉዓላዊ መብታቸውን ለመጠቀም ያላቸውን ፍላጎት ያሳየ ነው አሉ የአማራ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት።
የምክር ቤቱ ሰብሳቢና የአዴኃን ሊቀመንበር ተስፋሁን ዓለምነህ እንዳሉት የዜጎች የነቃ ተሳትፎ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጎለበተ መጥቷል፡፡
ድምፅ መስጠታቸውን ጠቁመው ምርጫው ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ እየተካሄደ ነው ብለዋል፡፡
የዴሞክራሲ ባሕል ግንባታው መሠረት እየያዘ መጥቷል ሲሉም ገልጸዋል፡፡

