Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በሚወዳደሩበት የጎማ 2 የምርጫ ክልል እየተካሄደ ያለው የምርጫ ሒደት ፍትሃዊ ነው – የተለያዩ ፓርቲዎች ዕጩዎች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሚወዳደሩበት የጎማ 2 የምርጫ ክልል እየተካሄደ ያለው የምርጫ ሒደት ፍትሐዊና ዴሞክራሲያዊ ነው አሉ የተለያዩ ፓርቲዎች ዕጩዎች፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በዕጩነት በቀረቡበት በጎማ 2 ምርጫ ክልል ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እየተፎካከሩ የሚገኙት ኢዜማ እና የነጻነትና እኩልነት ፓርቲ ዕጩዎ እየተካሄደ ያለው ምርጫ ፍትሐዊና ዴሞክራሲያዊ ነው ብለዋል፡፡
ከማለዳው ጀምሮ እየተካሄደ ያለው ምርጫ አስፈላጊ ሕጋዊ አሰራሮችን ተከትሎ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የተገኘውን ዕድል ዜጎች በፍትሐዊነትና በዴሞክራሲያዊ መንገድ እየተጠቀሙበት መሆኑን አንስተዋል፡፡
በጎማ 2 ምርጫ ክልል በአጠቃላይ 87 የምርጫ ጣቢያዎች የሚገኙ ሲሆን÷ በብልጽግና ፓርቲ ዕጩ ሆነው የቀረቡትን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጨምሮ አራት ፓርቲዎች ለምርጫ እየተፎካከሩ እንደሚገኙ ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
Exit mobile version