Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

እስካሁን ያለው የምርጫ ሒደት ፍፁም ነፃ እና ሰላማዊ ነው – የኢዜማ ፓርቲ የሰሜን ኢትዮጵያ አስተባባሪ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ፓርቲ የሰሜን ኢትዮጵያ አስተባባሪ አቶ ሃይለማርያም ብርሃኑ በባሕር ዳር ከተማ በመገኘት ድምፅ ሰጥተዋል።
አቶ ሃይለማርያም ብርሃኑ በሰጡት መግለጫ÷ የኢዜማ ደጋፊዎች፣ አባላትና አመራሮች በምርጫው ሒደት ላይ በመራጭነት፣ በአስመራጭነት እና በተመራጭነት ንቁ ተሳትፎ እያደረጉ እንደሚገኙ ገልፀዋል።
እስካሁን ባደረጉት ክትትል የምርጫው ሒደት ፍፁም ነፃ እና ሰላማዊ መሆኑን ያነሱት አስተባባሪው÷ ኅብረተሰቡ ይበጀኛል ያለውን አካል በካርዱ እየመረጠ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።
እስካሁን ያለው የምርጫ ሒደት መልካም መሆኑን ገልጸው÷ ምርጫ የስልጣኔ መገለጫ በመሆኑ ሁሉም ዜጋ ካርዱን በአግባቡ እንዲጠቀም አሳስበዋል።
Exit mobile version