Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በአማራ ክልል ኩታበር ምርጫ ክልል ተቋርጦ የነበረው የምርጫ ሂደት ዳግም ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል ኩታበር ምርጫ ክልል ተቋርጦ የነበረው የምርጫ ሂደት ዳግም ተጀምሮ መራጮች ድምፅ እየሰጡ ነው፡፡

በአማራ ክልል በኩታበር ምርጫ ክልል ሥር ከሚገኙ 73 ምርጫ ጣቢያዎች መካከል አንዱ በሆነው የቁንዲ -ለ- ምርጫ ጣቢያ ተቋርጦ የነበረው ምርጫ ዳግም ጀምሯል፡፡

በአሁኑ ወቅትም መራጮች በምርጫ ጣቢያው በመገኘት ድምፃቸውን እየሰጡ ይገኛሉ፡፡

የምርጫ ጣቢያው አስተባባሪ ሙሐመድ አሊ የምርጫው ሂደት ከረፋዱ 4 ሰዓት አካባቢ ለጥቂት ደቂቃዎች ተቋርጦ የነበረ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ግን ዳግም ተጀምሮ ምርጫው ቀጥሏል ብለዋል፡፡

Exit mobile version