Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ምርጫ ሀገር የምናስቀጥልበትና ዴሞክራሲ የምንለማመድበት ነው – ሙዓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ምርጫ ሀገር የምናስቀጥልበት እና የምናጸናበት፣ ዴሞክራሲ የምንለማመድበት ብሎም ለሀገር ዋጋ የሚከፍለው እና የማይከፍለው የሚለይበትም ጭምር ነው አሉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማሕበራዊ ዘርፍ አማካሪ ሙዓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ።

ሙዓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በምርጫ ክልል 28 በዛጎል ትምህርት ቤት አካባቢ የምርጫ ጣቢያ ተገኝቸው ድምጻቸውን ሰጥተዋል።

በዚሁ ወቅት ሙዓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፥ መራጩ ሕዝብ ከሌሊቱ 11 ሰዓት ጀምሮ ተሰልፎ ድምፅ በመስጠት ለምርጫው ያለውን ከፍተኛ ተሳትፎ አሳይቷል ብለዋል።

የመራጩ ሕዝብ በሌሊት በነቂስ ወጥቶ መምረጥ በሀገሩ ጉዳይ ላይ ያለውን የእኔነት ስሜት የሚገልጽና ሕዝቡ ለመምረጥ የማንም ቅስቀሳ እንደማያስፈልገው ያሳየ ነው ሲሉም ተናግረዋል።

#ኢትዮጵያ #ኢትዮጵያእየመረጠችነው #በምርጫብቻ #ፋናዲጂታል #Election #fanadigital #Ethiopia #Ethiopiavotes #Democracy #fanatelevision

Exit mobile version