Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ምቹ የውድድር ስነ ምህዳር የተፈጠረበት ነው – ተፎካካሪ ፓርቲዎች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ዞን የሚንቀሳቀሱ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ምቹ የውድድር ስነ ምህዳር የተፈጠረበት ነው አሉ፡፡

ይህን ያሉት የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ህብረት ፓርቲ እና የወላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ (ወብን) ፓርቲ ተወካዮች ናቸው፡፡

ተወካዮቹ ዜጎች ያለማንም ጣልቃ ገብነት በራሳቸው ፍላጎት ላመኑበት ፓርቲ ድምጽ እየሰጡ መሆናቸውን ታዝብናል ብለዋል፡፡

የምርጫ ሂደቱ ያለምንም ችግር እየተካሄደ መሆኑን ገልጸው÷ ምርጫው የዜጎች እኩልነት የተረጋገጠበት መሆኑን ተናግረዋል።

ለተፎካካሪ ፓርቲዎች ምቹ የውድድር ምህዳር የፈጠረ እና በርካታ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ያሳተፈ መሆኑ የዘንድሮውን ምርጫ ለየት እንደሚያደርገው ገልጸዋል፡፡

ሀገር የምትቆመው በምርጫና ምርጫ ብቻ እንደሆነም አስገንዝበዋል።

በማስተዋል አሰፋ

#ኢትዮጵያ #ኢትዮጵያእየመረጠችነው #በምርጫብቻ #ፋናዲጂታል #Election #fanadigital #Ethiopia #Ethiopiavotes #Democracy #fanatelevision

Exit mobile version