Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በመዲናዋ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የድምፅ አሰጣጥ ሂደት በስኬት ተጠናቅቋል

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በመዲናዋ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የድምፅ አሰጣጥ ሂደት በስኬት ተጠናቅቋል አለ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የምርጫ ኮማንድ ፖስት።

በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ድምጽ የመስጠት ሂደት ፍጹም ሠላማዊ እና ስኬታማ ሆኖ መጠናቀቁን ነው ኮማንድ ፖስቱ ያስታወቀው።

በምርጫው ዕለት ቀንም ሆነ ሌሊት ምንም አይነት ወንጀል አለመፈጸሙ ተገልጿል።

ድምጽ የመስጠት ሥርዓቱ በስኬት እንዲጠናቀቅ መራጩ ሕዝብ፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች፣ ዕጩዎች እና ታዛቢዎች ላበረከቱት አስተዋጽኦ እና ኃላፊነታቸውን በተገቢው ለተወጡ መላው የጸጥታ አካላት ኮማንድ ፖስቱ ምስጋና አቅርቧል።

የድምጽ አሰጣጡ ከተጠናቀቀበት ሰዓት ጀምሮ ድምጽ ቆጠራው መቀጠሉንም አስታውቋል።

ድህረ ምርጫ ያለው ሂደት በተመሳሳይ በስኬት እንዲከናወን ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል።

Exit mobile version