አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በኢትዮጵያ ታሪክ ከእስካሁኑ ምርጫዎች ሁሉ የተሻለና ለቀጣይ ተሞክሮ የተወሰደበት ነው አሉ።
የጋራ ምክር ቤቱ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ በማስመልከት በሰጠው መግለጫ፤ ምርጫው ነጻ፣ ሠላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በትብብር ተሰርቷል ብሏል።
ፓርቲዎች በነጻነት ተንቀሳቅሰው የፖሊሲ አማራጫቸውን ለህዝቡ ማቅረብ መቻላቸውን አስታውሷል።
በዚህ ሂደት የሚገጥሙ ችግሮችን በመነጋገር በዴሞክራሲያዊ መልኩ በመፍታት ምቹ የፖለቲካ ስነ ምህዳር መፍጠር መቻሉንም አንስቷል።
የጋራ ምክር ቤቱ ስራ አስፈጻሚዎች እንዳሉት፤ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በኢትዮጵያ ታሪክ ከእስካሁኑ ምርጫዎች ሁሉ የተሻለ ነው።
አሸናፊው ማንም ይሁን ማን ከአሸናፊው የፖለቲካ ፓርቲ ጋር በትብብር ለመስራት ዝግጁነታቸውን አረጋግጠዋል።
ምርጫው በስኬት በመጠናቀቁ ገልጸው፤ ለምርጫው ስኬት አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል።

