Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የምርጫ ውጤት…

በማንኛውም የምርጫ ሒደት ከዋና ዋና ግቦች መካከል አንዱ ውጤትን በአግባቡ አጠናቅሮ በወቅቱና በየደረጀው ለሕዝቡ ይፋ ማድረግ ነው፡፡

የምርጫ ውጤትን በየእርከኑ መግለጽ መራጩ እና የምርጫ አስፈጻሚዎች መካከል ያለውን ግልፀኝነት ያሳድጋል፡፡

ለዚያም ነው በምርጫ ጣቢያ፣ በምርጫ ክልል እና በማዕከል ተደራጅቶ በየደረጃው የመራጮች ድምጽ በአግባቡ ተቆጥሮ ይፋ የሚደረገው፡፡

የምርጫ ውጤት ሲገለጽ፡-

• የተመዘገበ የሕዝብ ብዛት፣

• በጠቅላላ ድምፅ የሰጠ ፣

• በትክክል ድምፅ የሰጠ መራጭ፣

• ድምፅ ያልሰጠ መራጭ፣

• የተበላሸ የድምፅ መስጫ ወረቀት፣

• ዋጋ አልባ የድምፅ መስጫ ወረቀትን ያካትታል፡፡

የምርጫ ውጤትን መግለፅ የሚችለው የምርጫ አስተዳዳር አካል ወይም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ብቻ ነው፡፡

ለምርጫ የቀረቡ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ወይም የግል ተወዳዳሪዎች ከምርጫ ቦርድ እውቅና ውጪ አሸንፌያለሁ ብለው ማወጅ አይችሉም፡፡

በምርጫ ጣቢያዎች እና በምርጫ ክልሎች የተለጠፈው የመራጭ ውጤትም ለሙሉ አሸናፊነት አያበቃም፡፡

ከምርጫ ጣቢያ ጀምሮ እስከ ምርጫ ክልል ያለውን የምርጫ ውጤት በቅብብሎሽ እስከ ማዕከል በማሰባሰብና በማደራጀት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ውጤቱን ደምሮ ካወቀ በኋላ አሸናፊውን አካል ለሕዝቡ ይፋ ያደርጋል፡፡

እርጅና፣ አካል ጉዳት፣ ሕመም፣ ኅዘን፣ ወሊድ፣ ሰርግ፣ ብርድ፣ ዝናብ፣ ፀሐይ፣ ጨለማ ያልበገራችሁ ኢትዮጵያውያን በቅድመ ምርጫ፣ በምርጫ እና በድህረ ምርጫ ወቅት ያሳያችሁትን ሰላማዊ የመንግሥት ምስረታ ፍላጎት፣ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ታዛቢዎች እንዲሁም ዓለም አቀፍ ተቋማትና ሀገራት ፍጹም ጨዋና ዴሞክራሲያዊ ስለመሆናችሁ እየመሰከሩላችሁ ይገኛሉ፡፡

ኢትዮጵያውያን ይሆነኛል ያላችሁትን ያለውክቢያ በፍላጎታችሁ በነጻነት መርጣችኋል፡፡

ምርጫ ቦርድ የምርጫ ውጤቱን ይፋ እስኪያደርግ በትዕግስት እንጠብቃለን፡፡

በምርጫው የተሳተፉ ተፎካካሪዎችም በቅድመ ምርጫና የምርጫ ዕለት ሂደቱ አሳታፊ፣ ሰላማዊ፣ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ ነው ስትሉ እንደነበረው፣ በድህረ ምርጫም ውጤቱ ሲገለጽ በጸጋ በመቀበል በምርጫ አሸንፏል ተብሎ በምርጫ ቦርድ ይፋ ከሚደረገው አካል ጋር ተባብሮ ሀገር የመሥራት ልምምድን እናዳብር፡፡

ኑ ሀገር እንሥራ!

Exit mobile version