Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በምርጫው የታየውን ሰላም በማስቀጠል ለዘላቂ ሰላም በጋራ እንቁም – የፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በምርጫው የታየውን ሰላም በማስቀጠል ለዘላቂ ሰላም በጋራ እንቁም አለ።

የጋራ ምክር ቤቱ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ፤ ምርጫው ሰላማዊ ሆኖ በመጠናቀቁ የተሰማውን ደስታ ገልጿል።

ልዩነቶቻችንና ችግሮቻችን በዴሞክራሲያዊ መንገድ በመፍታት በምርጫው የታየውን ሰላም በማስቀጠል የበኩላችንን ሚና በመወጣት ለዘላቂ ሰላም በጋራ እንቁም ሲል ጥሪ አቅርቧል።

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጸጥታ አካላት እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻዎችና ህዝቡ ምርጫው በስኬት እንዲጠናቀቅ ላደረጉት አስተዋጽኦ አድናቆቱን ገልጿል፡፡

Exit mobile version