አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ34ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተስተካካይ መርሐ ግብር ወላይታ ድቻ እና ነገሌ አርሲ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል፡፡
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ቀን 9 ሰዓት ላይ በተደረገው ጨዋታ ሁለቱም ቡድኖች ግብ ሳያስቆጥሩ ወጥተዋል፡፡
ሊጉን ሲዳማ ቡና በ61 ነጥብ ሲመራው መቻል በ53 ነጥብ 2ኛ እንዲሁም ነገሌ አርሲ በተመሳሳይ 53 ነጥብ በግብ ክፍያ ተበልጦ 3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡
አቤል ያለው በ14 ግቦች የሊጉን ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት ደረጃ ሲመራው ናትናኤል ዳንኤል በ13 ግቦች ይከተላል፡፡

