አዲስ አበባ፣ ግንቦት 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሶማሌ ክልል ሸቤሌ ዞን ቤረዓኖ ወረዳ የአነስተኛ የአውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት ግንባታ ሥራ ተጀምሯል፡፡
በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱላሂ መሐመድ እና የውሃ ቢሮ ኃላፊ አሕመድ ሚራድን (ኢ/ር) ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታው ከ90 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ እንደሚከናወን ተመላክቷል፡፡

