አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ የሚስተዋለውን ህገወጥ የሰዎች ዝውውር ለመግታት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በምርምር የታገዘ የመፍትሔ አማራጭ ሊያቀርቡ እንደሚገባ ተመላከተ፡፡
የፌደራል የህግና ፍትህ ኢንስቲትዩት ከሰመራ ዩንቨርሲቲ ጋር በመተባበር በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ዙሪያ ያዘጋጁት የምርምር ሲምፖዚየም ተካሂዷል፡፡
የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝደንት አብዱረህማን ከድር (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ የሀገርን የእድገት ጉዞ ለማፋጠን በምርምር የተደገፈ አሰራር ወሳኝ ነው፡፡
በአሁኑ ወቅት የሚስተዋለውን ህገወጥ የሰዎች ዝውውር ለመግታት ዩንቨርሲቲዎች በምርምር በመታገዝ መፍትሔዎችን የማመላከት ከፍተኛ ኃላፊነት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል፡፡
ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የሰላምና የምርምር ማዕከል ለማቋቋም በዝግጅት ላይ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በአመለወርቅ መኳንንት

