አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ተወዳጁና በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው ፋና 80 የውዝዋዜና ዳንስ ውድድር በምዕራፍ 5 በነገው ዕለት ይጀምራል።
በአዲስ አቀራረብና በአዳዲስ ጉዳዮች በሚጀመረው ውድድር መክፈቻ በምድብ አንድ የሚገኙ 8 የባህልና ዘመናዊ ዳንስ ቡድኖች ሥራዎቻቸውን ያቀርባሉ፡፡
በዘመናዊ ዳንስ ዘርፍ ነፀብራቅ፣ ቲ ተስፋ፣ ዩኒክ እና ዘውድ ዘመናዊ ዳንስ ቡድኖች እንዲሁም ኢትዮ ግዕዝ፣ ኬ ሀበሻ፣ ኢትዮ ወል እና አንድነት የባህላዊ ቡድኖች ወድድራቸውን ያደርጋሉ።
ቡድኖቹ በከፍተኛ ዝግጅት በሚቀርቡበት የመክፈቻ ውድድር ላይ ከመድረኩ ቀድሞ የሚሰናበተው ቡድን የሚለይ ይሆናል፡፡
የፋና 80 ምዕራፍ 5 ውድድር ነገ ከቀኑ 8:30 ጀምሮ በፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ለተመልካቾች ይደርሳል፡፡
በብርኽቲ ማህተመ

