Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

19ኛው የኢትዮጵያ ግማሽ ማራቶን ውድድር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 19ኛው የኢትዮጵያ ግማሽ ማራቶን ውድድር በአዲስ አበባ ከተማ መካሄድ ጀምሯል፡፡

መነሻና መድረውሻን መስቀል አደባባይ ባደረገው ውድድር በወንዶች 455፤ በሴቶች183 በድምሩ 638 አትሌቶች ተሳትፈዋል፡፡

ውድድሩ በዴንማርክ ኮፐንሀገን ለሚካሄደው የግማሽ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያን የሚወክሉ አትሌቶችን ለመምረጥና ተተኪዎንች ለማፍራት ያለመ ነው፡፡

ከ1ኛ እስከ 6ኛ ደረጃ ይዘው ለሚያጠናቅቁ አትሌቶች የገንዘብ፣ የሜዳልያና የዋንጫ ሽልማት እንደሚበረከተላቸው ተመላክቷል፡፡

Exit mobile version