Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሴቶች ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን ተጠቅመው በንቃት ተሳትፈዋል

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሴቶች ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን ተጠቅመው በንቃት የተሳተፉበት ነጻና ፍትሐዊ ምርጫ ነበር አሉ የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ማህበር ፕሬዚዳንት እናታለም እንዳለ ፡፡

ኢትዮጵያ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ያካሄደችውን 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የአፍሪካ ሕብረት፣ ኢጋድና የተለያዩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የምርጫ ታዛቢዎች ቡድን ተከታትለውታል፡፡

ምርጫውን ከታዘቡት 55 የሀገር ውስጥ ሲቪክ ማህበራት መካከል አንዱ የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ማህበር ነው፡፡

የማህበሩ ፕሬዚዳንት እናታለም እንዳለ እንዳሉት÷ ምርጫ ዜጎች መብታቸውን ተጠቅመው የሚበጃቸውን ፓርቲ የሚመርጡበት የዴሞክራሲ መገለጫ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታ የሁሉም ማሕበረሰብ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው÷ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሴቶች ንቁ ተሳትፎ የተረጋገጠበት የፖለቲካ ዓውድ ነበር ብለዋል፡፡

ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ፈቃድ በመውሰድ ሴቶች ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን ተጠቅመው በጠቅላላ ምርጫው ንቁ ተሳታፊ የሚሆኑበትን የሥነ ዜጋና የመራጮች ትምህርት መስጠታቸውን ተናግረዋል፡፡

ከ2 ሺህ በላይ አባላትን በማሰልጠን በዕለቱ የምርጫ ታዛቢዎች ተመድበዋል ያሉት የማህበሩ ፕሬዚዳንት ÷ በርካታ ዜጎች የመራጭነት ካርድ በመውሰው ድምጽ እንደሰጡ መጥቀሳቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ዜጎችን ያለማንም ጣልቃ ገብነት ሰላማዊ፣ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ድምፅ መስጠታቸውን ጠቁመው÷የሕዝቡን ተነሳሽነትና ፍላጎትም አድንቀዋል፡፡

Exit mobile version