Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶች ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ስኬት ንቁ ተሳትፎ ነበራቸው – ፌዴሬሽኑ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶች ፌዴሬሽን ግንቦት 24 ቀን 2018 ለተካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ስኬት የክልሉ ሴቶች ንቁ ተሳትፎ ነበራቸው አለ።

ፌዴሬሽኑ ምርጫውን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ፤ በክልሉ የተካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ በስኬት ተጠናቅቋል ብሏል።

የፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ወ/ሮ አለሚቱ ኃይለሚካኤል÷ ምርጫው ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ፍትሐዊ እና ነጻ መሆኑን ተመልክተናል ነው ያሉት።

ለዚህ ስኬት ሴቶች የነበራቸው ተሳትፎ ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰው፤ ፌዴሬሽኑ በምርጫው ሴቶችን በታዛቢነት ለማሳተፍ የተለያዩ ስልጠናዎችን መስጠቱን አስታውሰዋል።

2 ሺህ 953 ሴቶች በምርጫው በታዛቢነት ማሳተፍ መቻሉንም ጠቁመዋል።

የፌዴሬሽኑ ዋና ፀሀፊ ወ/ሮ ማስረሻ ዘሪሁን በበኩላቸው÷ ሴቶች በ2 ሺህ 630 የምርጫ ጣቢያዎች በቋሚነት እና በተንቀሳቃሽነት ምርጫውን በመታዘብ ኃላፊነታቸውን በብቃት መወጣታቸውን ተናግረዋል፡፡

በማቱሳላ ማቴዎስ

Exit mobile version