Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ፋና ላምሮት በፍጻሜ ዋዜማ ቅዳሜ ቀጥሎ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ላለፉት 11 ሳምንታት በጠንካራ ፉክክር የቆየው የፋና ላምሮት የምዕራፍ 22 ውድድር ቅዳሜ የፍጻሜ ዋዜማ ውድድሩን ያካሂዳል።

አምስቱ የቅዳሜ ተወዳዳሪዎች ዳንኤል አለልኝ፣ ኤርሚያስ መንግስቴ፣ ኤልያስ ገዛኸኝ፣ የአብሥራ ገዛኸኝ እና ቃለአብ ገዛኸኝ ከኮከብ ባንድ ጋር ለፍጻሜ ለማለፍ ይፋለማሉ፡፡

በምዕራፉ ፍጻሜ የሚቀሩ 4 ተወዳዳሪዎች የ1 ሚሊየን ብር ሽልማት ተዘጋጅቶላቸዋል፤ እነማን ወደ ፍጻሜው ያልፉ ይሆን?

ለፍጻሜ የሚደርሱ አራት ተወዳዳሪዎች ወደ 6ኛው የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር በቀጥታ የሚያልፉ ይሆናል፡፡

ቅዳሜ የፋና ላምሮት የምዕራፍ 22 የፍጻሜ ዋዜማ ውድድርን በቀጥታ ሽርጭት ልክ 6 ሰዓት ላይ ይጠብቁን፡፡

በለምለም ዮሐንስ

Exit mobile version