አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለምክክር ጉባኤው የተዘጋጁ አጀንዳዎችን ለፖለቲካ ፓርቲዎች በማቅረብ ግብዓት የመሰብሰብና የማረጋገጥ ስራ እያከናወነ ነው።
የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕ/ር) ለዚሁ በተዘጋጀው መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ኮሚሽኑ በአሁኑ ወቅት በአጀንዳ መቅረፅ፣ ማደራጀትና ማጠናቀር ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
በቅርብ ጊዜ ውስጥ ኮሚሽኑ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆኑን ጠቅሰው÷ ሥራው የተሳካ እንዲሆን የፓርቲዎች ተሳትፎ ወሳኝ ነው ብለዋል።
የፖለቲካ ፓርቲዎች ለሚከናወነው የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ እስካሁን እያደረጉ የሚገኘውን ጥረት አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በአንዷለም ተስፋዬ

