አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የዲላ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን በዛሬው ዕለት መርቀው ሥራ አስጀምረዋል፡፡
አቶ ጥላሁን ከበደ በዚህ ወቅት ÷ማዕከሉ የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥን ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር እንደሚያስችል ተናግረዋል።
ማዕከሉ በቴክኖሎጂ የተደገፈ፣ ብቃት ያለው፣ ፈጣንና ከሙስና የጸዳ የአገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓትን በመፍጠር የዜጎችን እርካታ እንደሚያሳድግ አስረድተዋል፡፡
ዜጎች በማዕከሉ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ከቤታቸው ወይም ከሥራ ቦታቸው ሆነው እንዲያገኙ የሚያስችል ዲጂታል አማራጭ የተዘጋጀለት መሆኑንም አመልክተዋል።
በክልሉ 3ኛ የሆነው ማዕከሉ 4 የፌደራል እና 5 የክልል ተቋማትን በውስጡ ያቀፈ ሲሆን÷ በአጠቃላይ 32 የተለያዩ የአገልግሎት ዓይነቶችን ለዜጎች ያቀርባል።
በማስተዋል አሰፋ

