Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የዓለም ዋንጫ የምድብ ጨዋታዎች ዛሬም ቀጥለው ይካሄዳሉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ ያዘጋጁት የ2026 ዓለም ዋንጫ ውድድር የምድብ ጨዋታዎች ዛሬም ቀጥለው ይደረጋሉ፡፡

የውድድሩ አዘጋጅ ሀገራት ካናዳ እና አሜሪካ የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን በዛሬው ዕለት የሚያደርጉ ይሆናል፡፡

ምድብ ሁለት ላይ የምትገኘው ካናዳ ምሽት 4 ሰዓት ላይ ከቦስኒያ ጋር ጨዋታዋን ታደርጋለች፡፡

ምድብ አራት ላይ የተደለደለችው አሜሪካ ደግሞ ሌሊት 10 ሰዓት ላይ ከፓራጓይ ትገናኛለች፡፡

ትናንት ምሽት በመክፈቻው ዕለት በተደረጉ የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታዎች ሌላኛዋ አዘጋጅ ሀገር ሜክሲኮ ደቡብ አፍሪካን 2 ለ 0 እንዲሁም ደቡብ ኮሪያ ቼክ ሪፐብሊክን 2 ለ 1 አሸንፈዋል፡፡

Exit mobile version