አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 24፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ)በአለም ዙሪያ የኮሮናቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 25 ሚሊየን ተሻግሯል፡፡
አለምን እየፈተነ ያለው የኮሮና ቫይረስ በቻይናዋ ከተማ ሁዋን ግዛት ከተከሰተ ወዲህ በየጊዜው በቫይረሱ የሚያዙ እና ህይወታቸው የሚያልፉ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ መምጣቱን መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
በዚህም እስካሁን ባለው መረጃ በአለም አቀፍ ደረጃ በቫይረሱ 25 ሚሊየን 170 ሺህ 439 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡
በተጨማሪም የ846 ሺህ 792 ሰዎችን ህይወት ቀጥፏል፡፡
ሆኖም ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥርም 17 ሚሊየን 510 ሺህ 604 መሆኑም ነው ከወርልድ ሜትር ያገኘነው መረጃ የሚያመላክተው፡፡
በአለም አሜሪካ፣ ብራዚል፣ ህንድ፣ ሩሲያ እና ፔሩ ቫይረሱ ከጸናባቸው ሃገራት መካከል ከአንድ እስከ አምስተኛ ደረጃን ይዘዋል፡፡

