Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሲዳማ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ35ኛ ሳምንት ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ሲዳማ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል፡፡
ቀን 9 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ኢትዮጵያ ቡናን 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡
ለሲዳማ ቡና የማሸነፊያ ግቦቹን ያሬድ ባየህ እና ብርሃኑ በቀለ ሲያስቆጥሩ÷ ኢትዮጵያ ቡናን ከሽንፈት ያልታደገች ግብ ዘላለም አባተ ከመረብ አሳርፏል፡፡
በተመሳሳይ ሰዓት በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ሌላኛው የዕለቱ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ መቻልን 3 ለ 0 ሲያሸንፍ ፍፁም ጥላሁን፣ ሀብታሙ ጉልላት እና የአብስራ ጎሳዬ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል፡፡
የሊጉ መርሐ ግብር ሲቀጥል ምሽት 12 ሰዓት ላይ ኢትዮጵያ መድን ከድሬ ዳዋ ከተማ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
Exit mobile version