አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ላለፉት 3 ወራት በጠንካራ ፉክክር ሲካሄድ የቆየው የፋና ላምሮት ምዕራፍ 22 የድምጻውያን ውድድር የፊታችን ቅዳሜ ሰኔ 13 ቀን 2018 ዓ.ም ፍፃሜውን ያገኛል።
ከ16 ተወዳዳሪዎች ጋር የጀመረው የፋና ላምሮት ምዕራፍ 22 ውድድር በየሳምንቱ አንድ ድምጻዊ እየተሰናበተ አራቱ ለፍጻሜ ደርሰዋል።
ውድድሩ በአንጋፋዎቹ ዛየን እና ኮከብ ባንዶች የተመራ ሲሆን÷ ዳኞች ለአስደናቂ የተወዳዳሪዎች አቅርቦት በተደጋጋሚ 10 ሺህ ነጥብ ሰጥተዋል።
አራቱ የፍፃሜ ተፎካካሪዎች የአብስራ ገዛኸኝ፣ ዳንኤል አለልኝ፣ ኤልያስ ገዛኸኝ እና ቃለአብ ገዛኸኝ ናቸው፡፡
ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ለዚህ የፍፃሜ ውድድር የ1 ሚሊየን ብር ሽልማት አዘጋጅቷል፡፡
አራቱ ተወዳዳሪዎች ለ6ኛው የአሸናፊዎች አሸናፊ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል፤ ማን የምዕራፍ 22 ኮከብ ሆኖ ያጠናቅቅ ይሆን?
ይህን ደማቅ ውድድር በቀጥታ ሥርጭት በመጪው ቅዳሜ ከ6:00 ጀምሮ በፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ሁሉም የሚዲያ አማራጮች ይከታተሉ።
በለምለም ዮሃንስ

