አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ከተካሄደባቸው የምርጫ ክልሎች መካከል የ723ቱ ውጤት ጸድቋል አለ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ።
የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ ዛሬ ምሽት በሰጡት መግለጫ እንዳሉት፥ የ501 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የ638 የክልል ም/ቤት ውጤቶች ተጠቃልለው ወደ ማዕከል ገብተዋል።
በአጠቃላይ ካሉት 1ሺህ 139 የምርጫ ክልሎች መካከል የ723ቱ የምርጫ ክልሎች ውጤቶች በቦርዱ መጽደቃቸውን ጠቁመዋል።

