Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የፋና ላምሮት ምዕራፍ 22 የድምጻውያን የፍፃሜ ውድድር የፊታችን ቅዳሜ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ላለፉት 3 ወራት በጠንካራ ፉክክር ሲካሄድ የቆየው የፋና ላምሮት ምዕራፍ 22 የድምጻውያን ውድድር የፊታችን ቅዳሜ ሰኔ 13 ቀን 2018 ዓ.ም ፍፃሜውን ያገኛል።

በፍፃሜ ውድድሩ ዳንኤል አለልኝ፣ የአብስራ ገዛኸኝ፣ ኤልያስ ገዛኸኝ እና ቃለአብ ገዛኸኝ በሦስት ዙር የመረጧቸውን ሙዚቃዎች ከዛየን ባንድ ጋር ያቀርባሉ።

ተወዳዳሪዎቹ ቅዳሜ በሶስት ዙር በሚያደርጉት ፉክክር አሸናፊው የሚለይ ሲሆን÷ ዛየን ባንድ ደግሞ የፍፃሜ ውድድሩን ይመራል።

በዕለቱ አንድ ተወዳጅ ድምፃዊ በክብር እንግድነት ይገኛል፤ ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ለእነዚህ ተወዳዳሪዎች የ1 ሚሊየን ብር ሽልማት አዘጋጅቷል።

እነዚህ አራቱ የምዕራፍ 22 የፍፃሜ ተወዳዳሪዎች ለ6ኛው የፋና ላምሮት የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር በቀጥታ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።

ማን የምዕራፍ 22 ኮከብ ሆኖ ያጠናቅቅ ይሆን?

ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን የቅዳሜውን የፍፃሜ ውድድር በፋና ዩቲዩብ እና ፌስቡክ ገጾች እንዲሁም በሁለቱም የፋና ቴሌቪዥን ቻናሎች በቀጥታ ሥርጫት ያስተላልፋል፡፡

አድማጭ ተመልካቾች ውድድሩን ቅዳሜ ከቀን 6:00 ጀምሮ በቀጥታ ሥርጭት በመከታተል በዕለቱ የሚገለጸውን የተወዳዳሪዎችን ኮድ በ8222 አጭር የጽሑፍ መልዕክት በመላክ እየተዝናኑ እንዲደግፉም ግብዣ ቀርቧል፡፡

Exit mobile version