Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

እስራኤል እና ሄዝቦላህ የተኩስ አቁም ለማድረግ ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) እስራኤል እና የሊባኖሱ ታጣቂ ቡድን ሄዝቦላህ የተኩስ አቁም ለማድረግ ተስማምተዋል፡፡

የተኩስ አቁም ስምምነቱ ሁለቱ ወገኖች ዛሬ ከማለዳ ጀምሮ የተኩስ ልውውጥ ማድረጋቸው ከተገለጸ በኋላ ነው፡፡

የተኩስ አቁም ስምምነቱ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ተግባራዊ መደረግ የጀመረ ሲሆን፥ በሁለቱ ወገኖች የሚደረገው የተኩስ ልውውጥ በጊዜያዊነት እንደሚቆም ተገልጿል፡፡

የእስራኤል ጦር ዛሬ ጠዋት በሄዝቦላህ በተፈጸመበት ጥቃት አራት ወታደሮቹ መገደላቸውን በመግለጽ በወሰደው የአጸፋ ጥቃት ከ80 በላይ የቡድኑ ኢላማዎች ላይ ርምጃ ወስጃለሁ ብሏል፡፡

እስራኤል ከእኩለ ሌሊት ጀምሮ በፈፀመችው ጥቃት 47 ዜጎች መሞታቸውን የሊባኖስ ጤና ሚኒስቴርን ጠቅሶ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

የእስራኤል እና ሄዝቦላህ ግጭት መቀጠሉ በአሜሪካ እና ኢራን የተደረሰው የሰላም ስምምነት ተግባራዊ እንዳይሆን እንቅፋት እንደሚፈጥር ሲገለጽ ቆይቷል፡፡

ዛሬ የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት በሊባኖስ ያለውን ግጭት ከማስቆም በተጨማሪ የአሜሪካ እና ኢራንን የሰላም ስምምነት በዘላቂነት ለማጽናት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ነው የተገለጸው፡፡

በሚኪያስ አየለ

Exit mobile version