Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሁሉም አሸናፊ የሚሆንበት የምክክር ጉባዔ ለማካሄድ የመገናኛ ብዙሃን ሚና…

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ሀገራዊ የምክክር ጉባዔ ሁሉንም አሸናፊ የሚያደርግ እንዲሆን መገናኛ ብዙሃን ሚናቸውን በአግባቡ ሊወጡ ይገባል አለ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን።
ኮሚሽኑ ለምክክር ጉባዔው ስኬታማነት የመገናኛ ብዙሃንን ሚና በተመለከተ የውይይት መድረክ እያካሄደ ነው።
የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አምባሳደር መሀሙድ ድሪር በዚሁ ወቅት እንዳሉት ፥ የምክክር ጉባዔው ከተለመደው አዘጋገብ በተለየ ለታሪክ የሚሰነድ በመሆኑ በአግባቡ ለሕዝቡ ማድረስ ይገባል።
ኮሚሽኑ የአጀንዳ ማሰባሰብ እንዲሁም የአጀንዳና የተሳታፊ ልየታ ሲያካሂድ መቆየቱን ገልጸው ፥ ሀገራዊ ጉባዔው ከመጪው ሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በ10 መሠረታዊ ጉዳዮች ላይ እንደሚካሄድ ጠቅሰዋል፡፡
ሀገራዊ የምክክር ጉባዔው ሁሉንም ኢትዮጵያውያን አሸናፊ የሚያደርግ እንዲሆን መገናኛ ብዙሃን ሚናቸውን በአግባቡ ሊወጡ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
መገናኛ ብዙሃን ተደራሽ የሚያደርጓቸው ዘገባዎች በተለይም የምክክር ሒደቱን አሳታፊነትና ገለልተኛነት ያረጋገጡ መሆን እንደሚጠበቅባቸው ተመላክቷል።
የሀገሪቱን መሠረታዊ ችግሮች ለመፍታትበሀገራዊ ምክክሩ የተገኘውን እድል ለማባከን የሚሰራጩ የተዛቡ መረጃዎችን በማጥራት ረገድ መገናኛ ብዙሃን ሚናቸውን እንዲወጡም ጥሪ ቀርቧል።
በኃይለማሪያም ተገኝ
Exit mobile version