Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በሶማሌ ክልል የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሐ ግብር ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሶማሌ ክልል የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት ተጀምሯል፡፡

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ በጅግጅጋ ከተማ የክረምት በጎ ፈቃድ መርሐ ግብር አካል የሆነውንና አነስተኛ ገቢ ላላቸው የሕብረተሰብ ክፍሎች የሚገነቡ የመኖሪያ ቤቶች ግንባታን አስጀምረዋል።

የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አካል ሲሆን፤ ለአቅመ ደካሞችና አነስተኛ ገቢ ላላቸው ዜጎች መጠለያ በመስጠት ረገድ ትልቅ እፎይታን እንደሚፈጥር ተገልጿል።

የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ለአቅመ ደካሞች ድጋፍ ለማድረግ፣ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብሮችን ለማፋጠንና የማህበረሰቡን አንድነት ለማጠናከር ያለመ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

በዚህ መርሐ ግብር የሚገነቡት 20 ቤቶች በዝቅተኛ ኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የከተማው ነዋሪዎችን የኑሮ ደረጃ የሚያሻሽሉ መሆናቸው ተመላክቷል።

ግንባታው ማህበረሰቡንና ወጣቶችን በበጎ ፈቃደኝነት በማሳተፍ እርስ በርስ የመረዳዳትና የአብሮነት እሴቶችን ይበልጥ ለማጠናከር ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ተጠቁሟል፡፡

ከክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በተጨማሪ ርዕሰ መስተዳድሩ እና የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ማከናወናቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

Exit mobile version