Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አርባምንጭ ከተማ ወደ ከፍተኛ ሊግ ወረደ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አርባምንጭ ከተማ ወደ ከፍተኛ ሊግ መውረዱ ተረጋግጧል፡፡

በ36ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ፋሲል ከነማ አርባምንጭ ከተማን 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡

በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ቀን 9 ሰዓት ላይ በተደረገው ጨዋታ የፋሲል ከነማን የማሸነፊያ ሁለት ግቦች ታምራት ኢያሱ አስቆጥሯል፡፡

ውጤቱን ተከትሎ አርባ ምንጭ ከተማ ቀሪ ሁለት ጨዋታዎች እያሉት ወደ ከፍተኛ ሊግ መውረዱ ተረጋግጧል።

አርባምንጭ ከተማ ከ2018 የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የወረደ የመጀመሪያው ክለብ ሆኗል።

በተመሳሳይ ሰዓት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ወላይታ ድቻን 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡

የኢትዮ ኤሌክትሪክን የማሸነፊያ ግቦች በረከት ወልደዮሐንስ እና አቤል ሀብታሙ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡

ወላይታ ድቻን ከሽንፈት ያልታደገውን ግብ ያሬድ ዳርዛ አስቆጥሯል፡፡

የሊጉ ጨዋታ ሲቀጥል በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ምሽት 12 ሰዓት ላይ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከሀድያ ሆሳዕና ይገናኛሉ፡፡

Exit mobile version